About Prophet Belay

ነቢይ  በላይ  የተወለደው  አማራ  ክልል ወሎ ክፍለ አገር ደሴ ከተማ ነው ፡፡ እናቱ ምንጫቸው ጎዣም ሲሆን አባቱ ደግሞ እዛው ወሎ ነው፡፡ ነቢዩ ወሎ ተወልዶ እድሜው ሰባት ዓመት ሲደርስ ወላጆቹ በቡና እርሻ ልማት ተግባር ተሰማርተው ወደ ሚዛን ተፈሪ ይዘውት ነጎዱ ፡፡ እድሜው አስራ አራት ሲሞላው ነቢይ በላይ ከዘላለም አዳኙ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ተዋወቀ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሄዶም  አልነበረ፡፡ ታሪኩ ከወዲሁ ነው፡፡እስቲ አብረን እንኖግዳለን፡፡

ሚዛን ተፈሪ ውስጥ ገብርኤል ቤተሰክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ መሪ ጌታ ሃያ ለሚሆኑ ልጆች የድቁና ትምህርት ያስተምራል፡፡ በአንድ መቃብርቤትውስጥ ዕለት ዕለት ከምሽቱ 11 ሠዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መሪ ጌታ ለእነ በላይና ለተቀሩት የእድሜ እኩዮቹ በሃይማኖት ጉዳይ ዙሪያ በትጋት ያስተምራል፡፡ እድሜ ለዛ መሪጌታ ብላቴናው በላይ የድቁና ትምህርቱን ተምሮ  ለማጠናቀቅ  በቃ፡፡  ብላቴናው  በላይ ምንም እንኳን መሰረታዊውን የድቁና ትምህርት ተምሮ  ሃይማኖት  አበውን  ጠንቅቆ  ለማወቅ ቢበቃም  ነፍሱ  በምን  ምክንያት  እንደሆነ አላውቅም በአንድ ጉዳይ ላይ ርሃብ ገጠማት፡፡ የሥላሴ    አንዱ    አካል    የሆነው    ወልድ እንዲገለጥላት         ነፍስያው         አጥብቃ ወተወተችው፡፡ ብላቴናው በላይ በዚህ የነፍሱ ታላቅ   ጥያቄ   ምክንያት   በውስጡ   እረፍት የሚባል  ነገር  አጣ፡፡  ሲነጋ  ኢየሱስን  ማወቅ ፈለገ፣  ሲመሽም  ኢየሱስን  ማግኘት  ተመኘ፣ ሌቱ   ሲያቅላላም   ኢየሱስን   ማየት   ጓጓ፡፡ ፈልጋው  በልቡ  ተደጋገመ፡፡  ለጊዜው  ቢሆን ይህን ርሃቡን የሚያስታግሰለት አላገኘም፡፡ የብላቴናው በላይ ኢየሱስንየማየት የፀና ምኞት መልኩን  ቀየረ፡፡  እንዲህም  ሆነ፡፡  ብላቴናው ማለዳ  ማለዳ  አባቱ  ወዳለሙት  የቡና  ጨካ ውስጥ   እየገባ   ድምጹን   ከፍ   በማድረግ ‹‹የማሪያም    ልጅ    ኢየሱስ    ሆይ    ላገኝህ እፈልጋለሁ፤ የማሪያም ልጅ ኢየሱስ ሆይ ላይህ እፈልጋለሁ››ይል ጀመር፡፡ አስገራሚው ነገር በዚህ ከባድ ርሃብ ውስጥ ነቢይ በላይ ሆኖ አንድ    ዕለት    አባትየው    ማታ    ከሌሎች ልጆቻቸው ጋር ነቢይ በላይን ጠርተው‹‹ አንተ ስታድግ ጳጳስ ትሆናለህ፤ ፍጻሜህ የሃይማኖት መሪ  ይሆናል››  አሉት፡፡  ወደ  በላይ  ታናሽ ወንድምም ዞር አሉና‹‹አንተ ደግሞ ሐኪም ትሆናለህ››   አሉት፡፡   አሁን   የነቢይ   በላይ ወንድም    የእንሰሳት    ህክምና    ዶክትሬት ዲግሪውን  አግኝቷል፡፡  ነቢይ  በላይ  ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ኮሌጅ ተመርቆ በነቢይነት ቅባት ሆሊ  ኢንተርናሽናል  ቤተክርስቲያንን  እየመራ ይገኛል፡፡    የአባቱ    ትንቢታዊ    የጳጳስነት ማህረግም ይኸው ነው፡፡ ገናም ነቢዩ ብዙዎችን በእግዚአብሔር ፀጋ ተደግፎ በፓፓነት መንፈስ ይመራቸዋል፡፡ አባትየው እስከ ዛሬ ድረስ በጌታ አይደሉም፡፡ዳሩ ግን የትኛው መልአክ ተገልጦ ይህንን   ታላቅ   ሚስጥር   እንደገለጠላቸው እስተዛሬ  ድረስ  አይታወቅም፡፡  ዝም  ብሎ በእግዚአብሔር ምህረትከመደነቅበቀር፡፡ የነቢይ በላይ ኢየሱስን የማግኘት ርሃብ እጅግ በዝቶ ሳለ አንድ ለሊት የ14 ዓመቱ ብላቴና ወጣት  ይህንን  ህልም  በመኝታው አልጋው ላይ ጋደም ብሎያያል፡፡ድንገት በሰመመን እንቅልፍ ውስጥ ሳለ በተኛበት አልጋላይ ሆኖ እንዲህ የሚልድምጽ ይሰማል‹‹አንተ ብላቴና ልብህ አጥብቆ እኔን  እንደፈለገ  ተረድቼዋለሁ፡፡ በየጫካው ውስጥ ሆነህ ስሜን እየጠራህ ተገለጥልኝ ያልከውን ድምጽ ሰምቼዋለሁ፡፡እኔን ማግኘ ትከፈለግህ የተማሪ ቤት መምህሮችህ የሆኑት መስፍንና ጥንፌጋር ሂድ፡፡ እነርሱጋር እንደሄድህ ለብዙ  ጊዜ  የፈለከኝን እኔን ኢየሱስን ይሰጡሃል››አለው፡፡ ይህ የጌታ ኢየሱስ ድምጽ በበብላቴናው በላይ ልብ ውስጥ ታላቅ ሀሴትንና ታላቅ እፎይታን አዘነበ፡፡   እነ መምህር መስፍንና ጥንፌ ቤት ለመሄድበእጅጉ ስለጓጓ ብላቴናው በላይ የተቀረውን የለሊት ሠዓታትያለ እንቅልፍ በመኝታ ስፍራው ላይ ሲገላበጥ እንደምንም አነጋ፡፡ ጠዋት ማለዳ አስራ ሁለትሠዓትላይ እነመምህር መስፍንና ጥንፌ ቤት በችኮላ እየሮጠ ይሄዳል፡፡ የመኖሪያ ቤታቸውን የውጭአጥር በር በእጁ ሲደበድብ የተደናገጠው መስፍን ከማለዳ የጸሎትሥፍራው ይነሳናበሩን ሲከፍት   ብላቴናው   በላይ   እያለከለከ ‹‹ኢየሱስን   ስጡኝ‹‹   ይላል፡፡   በጌታ የሆነው  መምህር  መስፍን  እዛው በቆመበት ክብሩን ለጌታይሰጥና ብላቴናውንይዞ ወደ ቤቱ ይገባል፡፡ መምህር መስፍን   ከጥንፌ ጋር ሆኖ ብላቴናውን  በላይ  እጁን  አዘርግተው በይፋ ጌታን እንዲያውቅና የግል አዳኙ አድርጎ እንዲቀበል አደረጉት፡፡

ነቢይ በላይ ጌታን ከተቀበለ በሦስተኛው ቀን ላይ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ የደህንነት ትምህርት በመማር ላይ ሳለ ድንገት አስገራሚ መለኮታዊ ገጠመኝ ውስጥ ገብቶ በራዕይ ሠማይ ተከፍቶ ጌታ ኢየሱስ  እርሱናሌሎች አዳዲስ አማኞች ወደሚገኙበት ጉባኤ ውስጥ ሲገባ አየ፡፡ ነቢይ በላይ በራሱ አንደበት ያንን ራዕይ እንዲህ ሲልይገልጸዋል፤‹‹ድንገት ሰማይ እንደበር   ተከፈተ፡፡   እጅግ   ውበትን የተላበሰ አንድ መልከ መልካም ሰው፣ ልብሱፍጹም ነጭ የሆነ በተከፈተው ሰማይ ውስጥ ወጥቶ ወደ እኛ ወረደ፡፡  በዛመካከል አንድ ሌላ ትልቅ እጅ ወደ  ወደ ኢየሱስ እየጠቆመ እንደዚህ አለ፡፡‹‹የምትፈልገው  ኢየሱስ  ማለት  እርሱ ነው›› አለኝ፡፡ በዚህን ጊዜውስጤ በከባድ የኢየሱስ ፍቅር ተሞላ፡፡ከዚህ ታላቅ ራእይ በኋላ ነቢይ በላይ የህይወት አካሄዱ በሙሉእየተለወጠ መጣ፡፡  ነገራ  ስራው  በሙሉ  የኢየሱስ ክርስቶስጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረሆነ፡፡ ጌታን መቀበሉን ያላወቁ ቤተሰቡ ሁሉ ከነቢዩ   ድርጊትና  አኋኋን   ተነስተው ‹‹ጴንጤ›› እንደሆነ ደረሱበት፡፡ ዕድሜው ያን ጊዜ አስራዎቹ መጨረሻላይ ነበር፡፡ አለም የምትፈልገውን የዕድሜ ክልሉን ለኢየሱስ ወዶ አስረከበ፡፡ ከዚህ የተነሳ ኢየሱስን በእውነት በሚከተሉ ቅዱሳን ላይ ይደርስ የነበረው መከራ በእርሱም ህይወት ውስጥይገለጥ  ጀመር፡፡ልጃቸው በላይ አንድ ቀን ጳጳስ እንደሚሆን ይተነብዩ የነበሩትወላጅ አባቱ እንኳን ሳይቀሩ ለተደጋጋሚ ጊዜ ሽጉጥ መዘዙበት፡፡ በቤተሰባቸው  ታሪክ  ውስጥ የመጀመሪያው‹‹ጴንጤ››የሆነው ይህ የእግዚአብሔር ሰው ኢየሱስን በራእይ ካየበት ከዛች ቅጸበት ጀምሮ‹‹ኢየሱስጌታ ነው››እና‹‹ሃሌ ሉያ››እያለ በሚጠራቸው ቃላቶቹ ሰይፍ ከየአቅጣጫው አስመዘዙበት፡፡

እየባሰ  ከመጣው  ነቀፋና  ስደት  የተነሳ ነቢይ  በላይ  አንድ  ቀን  አገር  ጥሎ፣ ከቀዬው ብርር ብሎ የሚጠፋበት አንድ የታሪክ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ አንድ ለሊት በመኝታው ተኝቶ ሳለ እንደ ልማዱአንድ መሳጭ ራዕይ ያያል፡፡አንድ ትልቅ የጦር አውሮፕላን ሙሉ በሙሉ ፈንጂ የታጠቀ በእርሱ ላይ ፈንጂ ጥሎ ሊያወድመው ይከታተለዋል፡፡ነቢይበላይ ከጦር አውሮፕላኑለማምለጥአብዝቶ ይሮጣል፡፡ እርሱ ሲሮጥ አውሮፕላኑም ሲከታተለው በመጨረሻአውሮፕላኑ ምን እንደነካው አይታወቅም ወደ ሌላ አቅጣጫ በፍጥነት እየበረረ   ሄዶ   ከአለት   ጋር   ተጋጨና እመሬት ላይ ተከሰከሰ፡፡ በዚህ መካከል ነቢይ  በላይ  በእፎይታ  መንፈስ  ውስጥ እያለከወሰደው የሰመመንእንቅልፍ ይነቃል፡፡ አስገራሚውና አስደንጋጩ ነገር ነቢይ በላይ ከእንቅልፉ ሲነቃ አባትየው የተኛበትን መኝታ ክፍልበዓይል ሰብረው ጎራዴ ይዘው ወደ መኝታ ቦታው መጡ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ነቢይ በላይ ራሱንበዛች ቅጽበትያገኘው አልጋ ስር ነበር፡፡ በራሱ አንደበት ነቢዩ ያንን ትውስታውን ሲያወጋ እንዲህ ይላል‹‹ስለእውነት አልጋ ስርማን ወስዶ   እንደከተተኝ   የማውቀው   ነገር የለም፡፡ አባቴጎራዴ ይዞ ሲገባ ያየሁት አልጋ ስር ተወትፌ ነበር፡፡ እዛው አልጋ ስር እያለሁ አባቴ በንዴት መንፈስ ሆኖ አልጋውን ከላይ አተረማመሰ፣ብርድ ልብሱንና    አንሶላውን    ወዲና   ወዲያ  ሲያንከራትት  እመለከት  ነበር፡፡  አባቴ በመጨረሻ በንዴት በሩን ዘግቶ ወደ መጣበት ተመለሰ፡፡ አሁንም እዛው አልጋ ሥር እያለሁ እንደገና እንቅልፍ ወሰደኝና ሌላ ራእይ ማየት ጀመርሁ፡፡ በትልቁ የቡና ጫካችን ውስጥ አባቴ አሁንም ጎራዴ ይዞ ሲያባርረኝ አየሁኝ፡፡  አባቴ ሲከታተለኝ እኔም ስሮጥ በመጨረሻም አንድ ቀጥ ያለ አስፋልትላይ በድንገት ከጫካው ወጥቼ ደረስኩ፡፡አስፋልትቁጥራቸውበዛያሉ ወጣቶች እጅ ለእጅ ተያይዘው ‹‹አመለጥኩኝ … አመልጥኩኝ›› የሚለውንየዘማሪትአዜብ መለሰንና‹‹አንተንካገኘ ሰው ምንይሆናል›› የሚለውን የዘማሪዮሴፍአያሌውን ዝማሬ እየዘመሩ ሲሄዱ አገኘኋቸው፡፡ በፍጥነት በእነርሱመካከልገብቼ ከእነርሱጋር እጆቼን አያይዤእኔም እንደነርሱእየዘመርኩወደፊት መሄድ   ጀመርኩኝ፡፡   ወደ   ኋላ   ዞር   ብዬ ስመለከት አባቴከኋላችን ቆሞ በእጁ ምልክት እየዛተብኝወደመጣበት ጫካ ተመልሶ ገባ፡፡ ይህ ሁሉየሆነው በህልሜ ነበር፡፡ እውነትም ማለዳ ስነሳ አባቴ ሊግድለኝፈለገ፡፡ እኔም በህልሜ እንዳየሁት ሮጬው ወደ አስፋልት በመሄድ አመለጥኩት፡፡

ነቢይ በላይ ከሚዛን ተፈሪ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ላይ ቀንናለሊትበልጅ እግሩ  እየኳተነ  ተጓዘ፡፡  ለአንዴና  ለመጨረሻ ጊዜ ከወላጆቹ ቤት በክርስትና ምክንያት ወጥቶ ለአብርሃም እንደተባለው ወደ ማያቀው አገር መጻተኛ ሆኖሊኖር ተሰደደ፡፡ከሚኖርበት መንደር አርባ ኪሎሜትር በእግሩተጉዞ አንድ የገጠር  ቀበሌ  ከደረሰ  በኋላ  ከመንገደኞች ሳንቲም ለማምኖ ጉዞውን ወደ ጅማ ከተማ አደረገ፡፡ጅማ ከተማ ከደረሰም በኋላ እንደገና ከሠዎች ጥቂት ብሮችለማምኖ ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ አደረገ፡፡  አዲስ አባ መጥቶ ዘመድ ወደሚሆኑት ሠዎች ዘንድ እንዲያስጠጉት ቢጠይቃቸውም‹‹አንተ ዘር አሰዳቢ ጴንጤ›› ብለው አበረሩት፡፡ ዘመዶቹ ለካ ቀድመው የዚህን ብላቴና ዘራቸውን ጴንጤነት ሰምተዋል! ነቢይ በላይ አዲስ አባባ መጥቶ ፍጹም መጠጊያ አልነበረውም፡፡ለገሃር ወደ ሚባል የአዲስ አባ ክፍልእንደውበዘፈቀደ መጥቶ ላይ ታቹን በጠራራ  ፀሐይ  ይንከራተት  ጀመር፡፡  በዚህ ሁነትውስጥ እያለ ሚኒባሶች ወደ ለገሃር መጥተው ውርውር ይሉጀመር፡፡ የሚኒባሶቹ ወያላዎች ‹‹ሞጆ ናዝሬት …ሞጆናዝሬት›› እያሉ ለመንገደኞች ጥሪ ሲያደርጉ ሰማ፡፡ ነቢይበላይ ኪሱ ገንዘብ ባይኖረውም እንዲህ የሚልድምጽ በውስጡ  ሰማ  ‹‹ሞጆ  …  ሞጆ››፡፡  በራሱ አንደበት  ያንን  ትእይንት  እያስታወሰ  ሲናገር ‹‹የዛን   ጊዜ   የመንፈስ   ቅዱስ   ድምጽ እንዴት  እንደሆነ  ባላውቅም  በውስጤ ሞጆ ሞጆ የሚልድምጽ አደምጥ ነበር›› ይላል፡፡ ነቢይ በላይ በውስጥ ነፍሱ የሰማውን ድምጽ ምናልባት የእግዚአብሔርይሆናል ሳይል አልቀረም በፍጥነት ሞጆ ሞጆ እያለ ወደሚጣራው ሚኒባስ ቀርቦ ሞጆ ለመሄድ ተሳፈረ፡፡ አንገቱንም  ወደ  ሹፌሩ  አስግጎ  ‹‹ሹፌር ሞጆ መሄድ እፈልጋለሁ፤ ነገርግን መሳፈሪያ ገንዘብ የለኝም››አለው፡፡ ሾፌሩ አስገራሚው ነገር ለቅጽበትም አላቅማማም፡፡‹‹ጩጩ አይዞሽ ችግር የለውም አርፈሽ ቁጭ በይ››አለው፡፡ እንደውም‹‹ምነው ርቦሻል እንዴ? ከንፈርሽ ደርቆ አመድ መስሏል››አለውና ጮርና ቄና  ሻይ  ገዛለት፡፡  ለነቢይ  በላይ ይሄ በዛን ወቅት በርሃብ አንጀቱ   ልክ እንደ ብሉይ ኪዳኑ መና ነበር፡፡ በፍጥነት የቀረበለትናመናተመገበ፡፡ በጌታም ምህረትና  ቸርነት  ጉዞውን  ወደ  ሞጆ ከተማ አደረገ፡፡

ሌላው የነቢይ በላይ ፈተና ሞጆ ከተማ ሲደርስ የሚቀበለው አንድም ዘመድ ወይም ባዳሰው አለመኖሩ ነው፡፡ በዛ የምጥ  ሠዓት  እኔ  ፀሐፊው እንደሚመስለኝ   ነቢይ   በላይ   እሞጆ ከተማ ጠራራ ፀሐይ ላይ ቆሞ እንዲህ ሲል የተቀኘ ይመስለኛል፡፡ እግዚአብሔር ያለው ምንይሆናል/ አምሮበት ሁሌ ይጓዛል / ሲጨነቅ አለም በምድር/ ደስ አለው ጻድቅ በእግዚአብሔር፡፡ ነቢይ በላይ በዛን ጊዜ ከደጓ ሚኒባስ ላይ ወርዶ እጠራራው ፀሐይ ላይ ብቻውን ቆሞ ሲያሰላስል አንዲት እራፊ ሀሳብ ወደ ልቡ ፈጠና ተሰነቀረች፡፡አገር ቤት ከወላጆቹ ጋር እያለ አባትየው አንድ ዕለት ሞጆ ስለሚገኘው ሙስሊም ሀብታም ዘመዱ ያወራው ነገር ታወሰው፡፡ ታዲያ የሰውየውን ስሙን እንጂ አድራሻውን በፍጹም አያውቅም፡፡ አሁንም ታናናሽ እራፊ   ሀሳቦች   እጠራራ   ፀሐይ   ላይ እየተጓዘ ከተፍ ከተፍ አሉለት፡፡የዛ የሙስሊም ዘመዱን ሙሉ ስም ያውቅ ነበርና  ወደ  አንድ  ሱቅ  ጎራ  ብሎ  ባለ ሱቁን‹‹ሼህ እከሌእንቶኔን›› ታውቃለህ ሲለው እንደአጋጣሚ ሆኖ ባለሱቁ ሙስሊሙን ሰውዬ ያውቀዋል፡፡ ይህ መልካምአጋጣሚለብላቴናው በላይ ቶምቦላ ነበር፡፡ጥቂት ተጉዞ ሙስሊም ዘመዱ ቤት ደረሰ፡፡ሙስሊም ዘመዱም ደግ ነበርና በሰላም ተቀበለው፡፡ ከእርሱም ጋር መኖር ጀመረ፡፡

አስደንጋጩ ነገርያደግ ሙስሊም ነቢይ በላይን አራት ቀን ካኖረው በኋላ አንድ ማለዳብድግብሎ‹‹እፈልግሃለሁ አንተ ልጅ››    አለውና  አንዲት  ጠባብ  ክፍል ውስጥ አስገብቶት‹‹ይኸውልህ እምነትህን በፍጥነት ቀይረህ ሙስሊም መሆን አለብህ፡፡ሙስሊም ከሆንክ እንደ ልጄ አድርጌ እቀበልሃለሁ፡፡ ከእኔም ጋር በሠላምና በተድላ ትኖራለህ›› አለው፡፡ ነቢይ በላይ በታዳጊ ስሜቱ እልህ ተናነቀው፡፡   ድምጹንም   ጮክ   አድርጎ ‹‹አልፈልግም፣ ከአባቴም ቤትኮብልዬ የወጣሁትኢየሱስ ጌታ ነው ብዬ ስለተናገርኩነው፡፡ የፈለገው ይቅርብኝ፡፡ የእኔ ሃይማኖትኢየሱስ ነው››ብሎ ለዛ ላስጠጋው ሙስሊም ሰውዬ መለሰለት፡፡ ሙስሊሙ ሰውዬእጅግ ተበሳጨ፡፡ወደ ልቡምተመልሶለብላቴናው በላይ ብዙ የማባበል   ቃል   ተናገረው፡፡   ታዳጊው ወጣት  ነቢይ  በላይ  ግን  በሀሳቡ  ፀንቶ ቀረ፡፡ ሞጆ በደረሰ በአምስተኛው ቀን እንደገና ወደ ሜዳ ወጣ፡፡ እዛው ሰፈር ወደሚገኙ  ወጣቶች  ዘንድ  ቀርቦ  የቀን ሥራ እንደሚፈልግ ነገራቸው፤ ወዲያውኑ ሞጆ  ከተማ  ውስጥ  ወደሚገኝ  የአረቦች ዶሮ እርባታ ውስጥ በቀን ሠራተኝነት ተቀጠረ፡፡    የዛኑ  ምሽት  ሞጆ  ከተማ ውስጥ በምትገኝ አንዲት ደሳሳ የአፈር ቤት ውስጥ በ30ብር በዱቤ ተከራይቶ መኖር ጀመረ፡፡በቀን ሠራተኝነት በማገልገል የተፈራረመው ስምንት የኢትዮጵያ ብር፡፡ አስገራሚው አንዳንዴም አሳዛኙ ነገር ወንድማችን  ነቢይ  በዛ  የአረቦቹ  ዶሮ እርባታ ውስጥ በስራ የቆየው ሁለትቀን ብቻ መሆኑ ነው፡፡የመጀመሪያው ቀን እንደማንኛውም ታታሪ የዶሮ እርባታው ሠራተኞች በማለዳ ገብቶ የተመደበለትን ተግባር እየተወጣሳለ ከቀኑ ስምንት ሠዓት አካባቢ የሞጆ ሀሩር ፀሐይ ራሱን አብዝቶ ስለመታው  ተነገዳግዶ  እዛፍ  ስር ተቀመጠ፡፡ እንደምንም የቀኒቱን ከራራ ፀሐይ በረድ ስትልለት ተመልሶ ወደ ተከራያት አፈር ቤቱ በአፉ ምግብ ሳይዞር ይሄዳል፡፡   በሁለተኛው   ቀን   በራበው አንጀቱ ወደዛ የአረቦቹ ዶሮ እርባታሄዶ የተመደበለትን የቀን ሥራ እየሰራ ሳለ በርሃብ የደከሙት እጆቹ ዒላማ ስተው በአንደኛውእጁላይ አስራ ሁለትቁጥር ሚስማር ተቸነክሮበት ከባድ የጣር ልቅሶ አለቀሰ፡፡ የሰውነቱ ደም በእጆቹ በኩል እንደ ጅረትቁልቁልወደ መሬትፈሰሰ፡፡ ዳሩ ግን በሦስተኛው ቀን ወደዛ ሥፍራ ለመሄድ     አልደፈረም፡፡ ምክንያቱም  የአረቦቹ የዶሮ እርባታ ሥፍራ መስሪያ ቤት ሳይሆን መሰሪያ ቤትሆኖ አግኝቶታልና፡፡ግራ የገባው የእግዚአብሔር ሰው ነቢይ በላይ በአስራ አምስት ዓመት ዕድሜው አልሆንለህ ያለውን የቀን ስራ እርግፍ አድርጎ እዛው በዱቤ በተከራየበት ቤት ውስጥ ስራውን ጾምና ፀሎት ያደርጋል፡፡  በጾም  ፀሎቱ  መካከል የእግዚአብሔር መልአክ የሆኑ ሠዎች ይመግቡታል፡፡አንድ ወር ያህል በከፊል ደመናማ ጾምና ፀሎት ውስጥ ሆኖ እንደከረመ  የቤቱ አከራይ አንድ ቀን ወደ እርሱ መጥተው ‹‹የቤት ኪራዩን ጉዳይ አታስብ፤ተከፍሎልሃል›› አሉት፡፡ሁለተኛ ወር ላይም እንዲሁ አከራዩ ወደ እርሱመጥተው‹‹የቤት ኪራዩን ጉዳይ አታስብ፤ተከፍሎልሃል››አሉት፡፡ነቢይ በላይ በራሱ   አንደበት   ስለቤት   ኪራዩ   ሲናገር ‹‹አምስት ዓመት ሞጆ ከተማ ስኖር አንድም ቀን የቤት ኪራይ ከፍዬ አላውቅም፤ እንዲያም ሆኖ ሞጆ ከተማ ውስጥ የችግር ጥግ የሚባለውን ኑሮ በደም ኖሬዋለሁ››ይላል፡፡

ነቢይ በላይበሞጆ ከተማ በኖረባቸው አምስት ዓመታት ውስጥ የዕለት ተግባሩ ሁሉ በጾምና በጾሎት  የተቃኘ  ሆነ፡፡  ጾሙ  አንዳንድ  ጊዜ መጠነ   አጥቶተዝለፍልፎ ይወድቅ ነበር፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላግን ወጣቱ የእግዚአብሔር ወደ አንድ ለማመን ወደ ሚከብድየ ምግብ ባርኮትውስጥይገባል፡፡ይህንን ድንቅባርኮት ከራሱአንደበት እንስማ፤‹‹ለሊት ለሊት ዘጠኝ ሰዓት አካባቢአንድ ሰውቢያነስ ለአንድዓመት ያህል  ፍትፍት  በሰሃን  እያመጣ  ይመግበኝ ነበር፡፡ያንን ሰው እጁን እንጂአካሉን አላይም ነበር፡፡በመጀመሪያ ሰሞንህልምይመስለኝ ነበር፡፡ ኋላግን በእርግጥእውን እንደሆነ ያረጋገጥኩትጠግቤ ከእጁከበላሁ በኋላውሃ እጠጣናአገሳነበር፡፡ያ እጅበዛየርሃብ ዘመኔ ያለማንም  እርዳታ  ራሱ  እያጎረሰኝ  የርሃብ ዘመኔን አሻግሮኛል››፡፡ ነቢዩ በአምስት ዓመታቱ የጾምና  የጸሎት  ዘመኑ  አስገራሚ የእግዚአብሔር  መገኘት  አራት  በአራት በሆነቺው የጭቃቤቱውስጥይሰማውነበር፡፡ የእግዚአብሔርመገኘትእንዴትባለ መልኩ ለነቢዩይገለጥእንደነበር ለጠየቅሁትጥያቄ ሲመልስልኝእንዲህ ብሎኛል፤‹‹ጉምየመሰለ ደመናጠባቧ ቤቴን ይሞላው ነበር፤በዛውስጥ የእግዚአብሔር መገኘት ይሰማኝ ነበር፤ እንዲሁም ግሩምየሆነየመዓዛሽታ ቤቴን ይሞላውና በዛመዓዛውስጥ እግዚአብሔር ድምጹንያሰማኛል፤አምስት ዓመቱየጾምና የጸሎትልምምዴ  ሊጠናቀቅ  ጥቂትወራቶች ሲቀሩኝእግዚአብሔርበእንግሊዘኛናበኦሮምኛ